Song Lyrics

አባቴ ኢየሱስ

Solomon Yirga
Meazaye Neh
አዝ፦ አቤት እርሱ ሲያውቅበት ኢየሱሴ አቤት ሲችልበት ከሞት አፋፍ ማውጣት ከጭንቀት ማሳረፍ (2x) የደረሰበት ያውቃል ተስፋው የጨለመበት በቃ አለቀ ብሎ ሞቱን ሲጠባበቅ ድል በድል አድራጊው ጌታዬ ደርሶለት ሳቅ በሳቅ ያረገው ከላዩ ገፎለት (4x) አዝ፦ አቤት እርሱ ሲያውቅበት ኢየሱሴ አቤት ሲችልበት ከሞት አፋፍ ማውጣት ከጭንቀት ማሳረፍ (2x) በምድረ በዳ ውስጥ አጋር እንዲያ ተጨንቃ ሲሞት እንዳታየው ልጇን አርቃ ጥላ ድምጿን አሰምታ በጣም አለቀሰች ማነው ሚደርስልኝ ኧረ ማነው አለች እግዚአብሔር ከሰማይ ድምጻቸውን ሰማ የጨለመውን ሕይወት እንደገና አበራ (4x) አዝ፦ አቤት እርሱ ሲያውቅበት ኢየሱሴ አቤት ሲችልበት ከሞት አፋፍ ማውጣት ከጭንቀት ማሳረፍ (2x) የሞት ፍርሃት መጥቶ ዙሪያዬንም ከቦኝ መሄጃ ማምለጫ ሁሉም ግራ ገብቶኝ ተጨንቄ ሳለሁ ጌታ ደርሶልኛል ሸክሜን አራግፎልኝ በደስታ ሞልቶኛል (4x) እንደሰው አይደለም (8x) ይገርመኛል እዚህ መድረሴ (2x) ይገርመኛል ሰው መሆኔ ይገርመኛል እኔ ማለፌ
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection