Song Lyrics

እሄዳለው

Ehedalew

Selam Desta
Alideraderim
እኔማ አለኝ ክብር (፪x) እኔማ አለኝ አክሊል (፪x) ለጽዮን ስብሰባ ተጠርቻለሁ ስራው በእኔ ተቆጥሮ ትገቢያለሽ ተብያለሁ ኩነኔ የለብኝም ከሳሼስ ማነው እርሱ በደሙ አጽድቆ ልጁ ተብያለሁ ከግብጽ ምድር ቢወጡ ወደ ተስፋይቱ ምድር ወደ ውቧ ከነዓን ቢጠሩ ብዙዎቹ ቀሩ ምድረ-በዳ ሳይደርሱ ሳይገቡ ከእርስታቸው/ከግባቸው ጋር ያ ተስፋ ከፊቴ ካለው ጋራ ፍጹም አይወዳደር የኔማ አዲሲቱ ነው እየሩሳሌም በበጉ ቅኔ በሙሴ ዜማ እዘምራለሁ ከመላዕክት ጋራ ክበር ክበር እያልኩ ፊቱ እቆማለሁ እርሱ ስለረዳኝ እኔ እዘምራለሁ እሄዳለሁ ልዘምር ወደላይ ወደላይ እጠራለሁ ልዘምር ወደላይ ወደላይ ከእነ አብርሀም ጋራ ከእነ ይስሀቅ ከእነ እስራኤል ጋራ ከእነ ቅዱሳን እሄዳለሁ ልዘምር ወደላይ ወደላይ እጠራለሁ ልዘምር ወደላይ ወደላይ
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection