Song Lyrics

በቂ ነው

Beqi New

Selam Desta
Alideraderim
በጣም የከበረ እጅግ ያየለ ከወርቅ እንቁ ይልቅ የተሻለ በፍፁም ድርድር አብ የማያውቅበትን አንድያ ልጁን/ክንዱን ሰጠ ኢየሱስን አዝ፦ በቂ ነው ከበቂም በላይ (፫x) ለሰማይ ቢሉ ለምድሩም ሲሳይ ስቀበለው ያኔ እንደግል አዳኝ መዘገበው ስሜን በላይኛው ሰማይ የቅዱሳን ተስፋ በረከቴ ሆኖኛል ፡ ቀረኝ የምለው የለም አብ ጨርሶ ባርኮኛል ስቀበለው ያኔ እንደግል አዳኝ መዘገበው ስሜን በላይኛው ሰማይ የቅዱሳን ተስፋ ስጦታዬ ሆኖኛል ቀረኝ የምለው የለም አብ ሁሉንም ሰጥቶኛል ከዚህ በላይ ባርኮት ምናለ ከዚህ በላይ በላይ ከዚህ በላይ ደስታስ ምናለ ከዚህ በላይ በላይ ከዚህ በላይ ሰላም ምናለ ከዚህ በላይ በላይ አለም የሌላትን አገኘሁ ከላይ ከሰማይ ዓሣ በምድር/በየብስ ላይ ሕይወት አያምረው ከባህር እርቆ መኖር አያሰኘው ሁልግዜ መገኛው አንድ እና አንድ ነው ከውሀ የወጣ እለት መሞቻው ቅርብ ነው የእኔም ያለኢየሱስ ልክ እንዲህ ባዶ ነው ከመገኛ እርቆ መኖር ኧረ እንዴት ከንቱ ነው የሕይወት እንጀራ ጠግቤ የሕይወት ውሀ ረክቼ ከእርሱ ወዴት እሄዳለሁ መገኛዬ አንድ እና አንድ ነው በረከቴ ኢየሱስ ብቻ ነው አዝ፦ በቂ ነው ከበቂም በላይ (፫x) ለሰማይ ቢሉ ለምድሩም ሲሳይ
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection