Song Lyrics

ናና ሙሽራዬ

Selam Desta
Alideraderim
ሰፊው ሜዳ ተጠናቆ የጅረት ጉዞ ተገባዶ በባከነ ሰዓት እንዳለሁ ዘመኑ ይነግራል የሚሆነው አስረግጦ በቃ ልንቃ ላብራ መብራቴ ላሰናዳ ይመር ጎጆዬ ሙሽራዬ እንዳትቆም ከደጄ ናና ሙሽራዬ ናና ኢየሱስ ጌታዬ በህብረት ሲጠብቊ ቆነጃጂቶች በናፍቆት ከልባቸው አንተን ሊያዩ ፈላጊዎች ይሁን እንጂ በአምስቱ ስንፍና ይታያል ከመቅረዛቸው ዘይት ጎሎ ማብራያቸው ጨልሟል አንድ ቀን ተነፋ መለከት የጠበቁት ከሰፈር ገባ ድንገት ሊሸምቱ በወጡበት ገባና አላውቅም አለ ደጁንም ዘጋና በቃ ልንቃ ላብራ መብራቴን ላሰናዳ ይመር ጎጆዬ ሙሽራዬ እንዳትቆም ከደጄ በሩን ልክፈት ልነሳና ማልጄ ናና ሙሽራዬ ናና ኢየሱሱ ጌታዬ ሚታየው ሚሰማው ሚሆነው በአለም መምጣቱን ያሳያል አርጅቷል ይህ አለም ፍጥረታት በሙሉ በእርኩስት ተሞልቷል እግዚአብሔር የለም ባይ ቁጥር እጅግ በዝቷል የአለምን ለምን ልሻ እርሷም ዝጋለች የሰማዩን መንግሥት ነብሴም ናፍቃለች የአለምን ለምን ልመኝ እርሷም ዝጋለች የሰማዩን መንግሥት ነብሴም ናፍቃለች ናና ሙሽራዬ ናና ኢየሱስ ጌታዬ
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection