ስለበደላችን ደቀቀ ስለኃጥያታችን ቆሰለ ስለመተላለፋችን ሞተ በመገረፉ ቁስል ፈወሰን በቀራኒዮው ስፍራ በመስቀል የሞተው በእሾህ ሲጎነጉኑ ደሙ የፈሰሰው በጦር ጎኑን ሲሉ በአለንጋ ሲልጡ ዝም ማለቱ ለእኛ ነው መራራን ሲያጠጡ ፍጹም አላፈረም እርቃኑን ሲታይ ሰለ እኛ ለአለም ስሙ ይክበር ዘላለም ይንገስ ወልድ እግዚአብሄር በእራስ ቅሉ መንደር የፈሰሰው ደሙ ንጹህ ነው ያለዋኖስ ያለበጐች ደም የአለምን በደል ጠረገው ደሙን ይዞ ገባ ወደ አባቱ አወረደ ከላይ ምሕረቱን አመጻችን ሁሉ ተወግዶ ተቆጠረ በእኛ ላይ ፅድቁ ፍጹም አላፈረም እርቃኑን ሲታይ ሰለ እኛ ለአለም ሥሙ ይክበር ዘላለም ይንገስ ወልድ እግዚአብሄር እጅጉን በችንካር አጥብቀው ወጠሩ ጀርባውን በጅራፍ እያቆሰሉ የአለማት ፈጣሪን ያለእፍረት ቢንቁ ጸሀይ እና ጨረቃ እርሱን አከበሩ በምሕረቱ ነው ባለጠጋ እኛን ሊምር ወደደ ጌታ እኛን አለ ሩሃማ (፪x) እኔን አለ ሩሃማ (፪x)