Song Lyrics

ና ጌታ ይወድሃል

Na Geta Yiwedehal

Selam Desta
Alideraderim
እርቆ ለጠፋ ድርሻውን ይዞ ከአባቱ ቤት ኮብልሎ ወደ ምኞት ጉዞ እጅግ ክፉን ቢያደርግ ቢሆን ተላላ ነፍሱን አልጠቀመም ከፍቶታል በጣም አንድ ቀን ሲመለስ ወደ ልቡ ሀሳቡን ሰብስቦ ሲቃኝ አባቱን ይኖር ነበረ በደስታ ፡ አሁን ግን ገብቶታል መሆኑ ጎስቋላ እንደ ልጁ ባያየኝ እንኳን ልሁን እንደ ባሪያ ብሎ ለወሰነ ለቆረጠ ጀግና ገና ሳይገባ ወደ መንደሩ ፡ አባቱ አቀፈው በፍቅር እጁ/ልክ እንደበፊቱ ና ና ና ጌታ ይወድሀል ና ና ና ደጁ ላይ ቆሞ ይጠራሀል ና ና ና ውዴ ይወድሀል ና ና ና ደጁ ላይ ቆሞ ይጠራሀል ሁሉ እንዲመለስ በንስሀ ወዶ ይታገሳል ጌታ ዝምታው በኃጥያት አይደለም ማለት በርታ ቀን እጅግ ሳይከፋ ሳይመጣ የጥፋት ውሀ እንዳን በልጁ ግባ ወደ መርከቡ መርከብ ኢየሱስ ነው ማምለጫ መርከብ ወጀቡ ቢያልም ፍፁም አትሰጋበት ና ና ና ጌታ ይወድሀል ና ና ና ደጁ ላይ ቆሞ ይጠራሀል ና ና ና ውዴ ይወድሀል ና ና ና ደጁ ላይ ቆሞ ይጠራሀል ቢጠላ እንጂ ሀጥያትን ኃጥያተኛን ከልቡ ይወዳል ይሉት የለ ወይ ቀድሞም እርሱ ከአመጸኞች ጋር ይወዳጃል መሪ አጥተው ለተበተኑ እውነተኛ እረኛ ነው ይሰበስባል በፍቅር እጁ አቅፎ ያሞቃል በእቅፉ
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection