Song Lyrics

ተመርጫለው

Selam Desta
Alideraderim
ተመርጬአለው እኔ ተወድጃለው እኔ ጸድቄአለው በርሱ እንድኖርለት ለርሱ(*2) ጸጋው በእምነት አድኖኝ ኢየሱስ ጽድቁን አልብሶኝ ስለኔ በአብ ፊት ታይቶ ፈጽሞታል ስራዬን ጨርሶ(*2) ሃሌሉያ*2 ጸጋው አቁሞኛል ሃሌሉያ*2 ምህረቱ አኑሮኛል ሃሌሉያ*2 ቸርነቱ በዝቶልኛል ሃሌሉያ*2 ለዚህ ጌታ ክብር ይገባዋል ለዚህ ጌታ ክብር ይገባዋል ለዚህ ጌታ ስግደት ይገባዋል ለዚህ ጌታ ልዕልና ይገባዋል ለዚህ ጌታ አምልኮ ይገባዋል ገና ከፍጥረት በቁጣ ነበርኩኝ በበደሌ ምክንያት ሙት የሆንኩኝ በኃጢአቴ መብዛት ሙት የሆንኩኝ(*2) ግን በምህረቱ ባለጠጋ ስለሆነ ከኢየሱስ ጋር ህይወትን ለኔ አደለ ግን በምህረቱ ባለጠጋ ስለሆነ ከኢየሱስ ጋር ህይወትን ለኔ እንኪ አለ ሃሌሉያ*2 ጸጋው አቁሞኛል ሃሌሉያ*2 ምህረቱ አኑሮኛል ሃሌሉያ*2 ቸርነቱ በዝቶልኛል ሃሌሉያ*2 ለዚህ ጌታ ክብር ይገባዋል ለዚህ ጌታ ክብር ይገባዋል ለዚህ ጌታ ስግደት ይገባዋል ለዚህ ጌታ ልዕልና ይገባዋል ለዚህ ጌታ አምልኮ ይገባዋል
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection