ምን አቃተህና ማህተሙን ፈትተሀል ሰባቱን ጥቅል መጽሐፍ ልትከፍት ችለሀል እንቆቅልሽ ፈቺ በማደሪያህ አለህ በዙፋን ላይ ሆነህ ሁሉን ታድሳለህ አቤቱ ውበትህን ማን ይመዝነዋል የዳዊት ስር እና ዘር ስግደት ይገባሃል በማደሪያህ ላይ አለህ/3 ሁሉን ታደርግ ዘንድ ቻይ ነህ በችሎትህ ላይ አለህ/3 ሁሉን ታደርግ ዘንድ ቻይ ነህ አልፋና ኦሜጋ ፊተኛ ኋለኛ ጅማሬህ አይታወቅ ያንተ መጨረሻ ገደብ ልክ የሌለህ ሀያል የእኛ ጌታ በግርማ ሞገስህ ሁሉን የምትረታ አቤቱ ውበትህን ማን ይመዝነዋል የዳዊት ስር እና ዘር ስግደት ይገባሃል የሞትና የሲኦል መክፈቻ በእጅህ ነው በላይ ቢሆንም በታች ስልጣን ያንተ ነው አዶናዩ ጌታ ምንስ ይሳንሀል ቋጠሮውን ልትፈታ ብቻህን ችለሀል አቤቱ ውበትህን ማን ይመዝነዋል የዳዊት ስር እና ዘር ስግደት ይገባሃል በማደሪያህ ላይ አለህ/3 ሁሉን ታደርግ ዘንድ ቻይ ነህ በችሎትህ ላይ አለህ/3 ሁሉን ታደርግ ዘንድ ቻይ ነህ በረከት እና ክብር ጥበብም ምስጋና ለታረደው በግ ይሁን ለዚያ ለገናና ሰቃይን እና ችግር መከራን ያስረሳ ኢየሱስ ብቻ ነው የይኁዳ አንበሳ አቤቱ ውበትህን ማን ይመዝነዋል የዳዊት ስር እና ዘር ስግደት ይገባሃል በማደሪያህ ላይ አለህ (፫x) ሁሉን ታደርግ ዘንድ ቻይ ነህ በችሎትህ ላይ አለህ/3 ሁሉን ታደርግ ዘንድ ቻይ ነህ