አብልጬ/አብዝቼ እንድወድህ አብዝቼ/አብልጬ እንዳፈቅርህ አንተን ከመካድ ይልቅ እራሴን እንድክድ ፀጋህ ይርዳኝ ፀጋህ ይርዳኝ እኔ እንኳን በአቅሜ እጅግ ደካማ ነኝ ሞት ቢሆን እስራት አንተን ለሚያገኝህ እኔ እራሴን እሰዋለሁ ከአንተ አይበልጥብኝም ብሎ ፊትህ እንዳላለ በገረድ ፊት ካደህ ፀጋህ/ኃይልህ ዳግም አቆመና ስለአንተ መስካሪ/ሰባኪ አረገው ፀጋህ ይርዳኝ ፀጋህ ይርዳኝ እኔ እንኳን በአቅሜ እጅግ ደካማ ነኝ ብዙ ፍቅርን መግለጥ በአፌ መቻሌ ለተግባር ፈጥኜ/ቸኩዬ ግን አንተን መካዴ ከአንተ ያነሰን ነገር ማድነቄ ቀርቶ እንድወድህ ፀጋህ ይርዳኝ አብዝቶ ፀጋህ ይርዳኝ ፀጋህ ይርዳኝ እኔ እንኳን በአቅሜ እጅግ ደካማ ነኝ ውድህ ያረከኝን አንተን ውዴ እንዳደርግህ ከነፍስህ/ከክብርህ በላይ የወደድከኝን እንድወድህ ጸጋህ/ሀይልህ በረዳኝ መጠን እንድቀርብህ እኔም እሻከሁ የእውነቴን ልወድህ/ልመስልህ ፀጋህ ይርዳኝ ፀጋህ ይርዳኝ እኔ እንኳን በአቅሜ እጅግ ደካማ ነኝ