አንተን እየሰጋሁ እኔን ያመንኩበት እየጠረጠርኩህ በእኔ እርግጥ የሆንኩበት ለካ የከንቱነት የሞኝነት ዘመን ነው ዛሬ ግን ነቅቼ እምነቴ ነህ እላለሁ ለካ የከንቱነት የሞኝነት ዘመን ነው ዛሬ ግን ሲገባኝ ሕይወቴ ነህ/ማኅተሜ እላለሁ (፪x) አንተ እምነቴ ነህ (፭x) ኢየሱስ ሕይወቴ ነህ አንተ ተስፋዬ ነህ (፪x) አንተ ማህተሜ ነህ (፪x) አንተ ሕይወቴ ነህ ኢየሱስ እምነቴ ነህ ባለማወቅ ጠንቅ በልበ ደንዳናነት የጨለምኩ ይህን ዓለም ለሚገዛ ለክፉ መንፈሥ ባሪያ ነበርኩ በዘላለም ቁጣ ተጥዬ ከአብ ሕይወት የራቅኩኝ ገና ከፍጥረቴ ሙት ነበርኩኝ የማመጣው የዋኖስ ደም አይደለም ያነፃኝ አብን እንዳየው ጸጋህ ነው የረዳኝ የማመጣው የበግ ደም አይደለም ያነፃኝ አብን እንዳምነው ጸጋህ ነው የረዳኝ በቃ ዳንኩኝ በሥራህ በቃ ዳንኩኝ በአቅምህ ለእኔ መዳኛ ነው ጸጋህ በቃ ዳንኩኝ በሥራህ በቃ ዳንኩኝ በአንተ አቅም ለእኔ መዳኛ ነው መሞትህ ለእኔ መዳኛ ነው ስራህ ለእኔ መዳኛ ነው ትጋትህ በደሌን ተሸክመህ ለዓለም እና ለአብ አንዴ ታይተሀል ፅድቅን አልብሰህ ለዘላለም በቀኙ አኑረሀል መልከጼዴቄ ባንተ እኔ ዳንኩኝ ከአቤል ደም ባየለ በደምህ ነፃሁኝ ከከንቱ እሩጫ ባንተ ታቅቤ ሞት ላይከጅለኝ መንደር ቀይሬ በምሕረትህ ብርታት ከጠላት ኮበለልኩ ከድካሜ ይልቅ ሃይልህንም አመንኩ በቃ ዳንኩኝ በሥራህ በቃ ዳንኩኝ በአንተ አቅም ለእኔ መዳኛ ነው ፀጋህ በቃ ዳንኩኝ በሥራህ በቃ ዳንኩኝ በአንተ አቅም ለእኔ መዳኛ ነው መሞትህ ለእኔ መዳኛ ነው ስራህ ለእኔ መዳኛ ነው መሞትህ ለእኔ መዳኛ ነው ፀጋህ ለእኔ መዳኛ ነው መሞትህ