Song Lyrics

ክብር ይሁን

Samuel Tesfamichael
Yemigermegn Medane New
አዝ፦ ከአንተ በቀር ብዙ ብዙ ብዙ ብዙ ጌቶች ገዝተውን ነበር እኛስ አላየንም እንደአንተ የሚሆን እጅግ ወደንሃል ለዘለዓለም ግዛን (2x) ክብር ይሁን ከክብርም በላይ ሞገስ ከሞገሥም በላይ ጌታ ነህና ኤልሻዳይ (2x) ሃሳብህ የሰላም ነው ሁልጊዜ ለሕዝብህ አላማህ ፍቅር ነው ጌታ ለልጆችህ የልብህ እርካታ ሰዎችን ማዳን ነው በቤትህ መኖር ጌታ ሕይወትን ማትረፍ ነው (2x) አዝ፦ ከአንተ በቀር ብዙ ብዙ ብዙ ብዙ ጌቶች ገዝተውን ነበር እኛስ አላየንም እንደአንተ የሚሆን እጅግ ወደንሃል ለዘለዓለም ግዛን (2x) ክብር ይሁን ከክብርም በላይ ሞገስ ከሞገሥም በላይ ጌታ ነህና ኤልሻዳይ (2x) ለጥያቄዎች ሁሉ በቤትህ መልስ አለ ለሁሉም እንደአመሉ ትናገረዋለህ ወደ አንተ የመጣ ማነው ሳያርፍ የሄደ ቤትህን ወደድነው ጌታ/ኢየሱስ ለሁሉም ዕረፍት አለ (2x) አዝ፦ ከአንተ በቀር ብዙ ብዙ ብዙ ብዙ ጌቶች ገዝተውን ነበር እኛስ አላየንም እንደአንተ የሚሆን እጅግ ወደንሃል ለዘለዓለም ግዛን (2x) ክብር ይሁን ከክብርም በላይ ሞገስ ከሞገሥም በላይ ጌታ ነህና ኤልሻዳይ (2x) ለእርስትህ የምትራራ ሕዝብህን ምታከብር ለጠላት መላገጫ አሳልፈህ አትሰጥም እንዳንተ የሚሆን መልካም ትሁት እረኛ በሕይወት ዘመናችን ኢየሱስ አላየንም እኛ (2x) አዝ፦ ከአንተ በቀር ብዙ ብዙ ብዙ ብዙ ጌቶች ገዝተውን ነበር እኛስ አላየንም እንደአንተ የሚሆን እጅግ ወደንሃል ለዘለዓለም ግዛን (2x) ክብር ይሁን ከክብርም በላይ ሞገስ ከሞገሥም በላይ ጌታ ነህና ኤልሻዳይ (2x)
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection