ክብር ይሁንለት ለንጉሡ ወደ ማደሪያው ይግባ ወደመቅደሱ (2x) ክበር ክበር ክበር በምሥጋና እጅግ ለተፈራው ለሆነው ገናና (2x) በመቅደሱ ምሥጋናዬን አሰማለሁ በተራዬ ከሚፈሩት ቅዱሳኑ ጋር እለዋለሁ ክበር በመቅደሱ ምሥጋናዬን አሰማለሁ በተራዬ ከሚፈሩት ቅዱሳኑ ጋር እለዋለሁ አምላኬ ክበር ክበር የእኔ ጌታ ክበር ክበር ለዘለዓለም ክበር ክበር ሁልጊዜ ክበር ክበር ለዘለዓለም ክበር የምህረት ደጁ ለእኔ ተከፍቶ አየሁ የንጉሥ ዘንግ ደግሞ ተዘርግቶ ከጨለማው ገዢ ነጥቆ አውጥቶ ወደ ፍቅሩ መንግሥት አስገባኝ ጐትቶ (2x) ሃሌሉያ አሃ (4x) ሃሌሉያ አሃሃ (4x) በምህረቱ ገባሁ ማን ሊከለክለኝ ኢየሱስ ቤዛዬ አዳኝ ስለሆነኝ ቅዱሱ ባለበት በውስጠኛው ስፍራ አገልጋይ አደረገኝ ስሙን እንድጠራ (2x) ምህረቱ ከቦኛል በቅዱስ ደሙ አንጽቶኛል ታዲያ ማነው የሚቃወመኝ ኢየሱሴ ካጸደቀኝ ምህረቱ ከቦኛል በቅዱስ ደሙ አንጽቶኛል ታዲያ ማነው የሚኮንነኝ ኢየሱሴ ካጸደቀኝ ሃሌሉያ አሃ (4x) ሃሌሉያ አሃሃ (4x) ኦሆ ኦሆ ኦሆሆ ሃሌሉያ አሃሃ (4x)