Song Lyrics

ክበር በሉት

Samuel Tesfamichael
Misale Yeleleh
ዓይኖቼን ወደተራሮች ባቀና ረዳቴ ይመጣል ብዬ ደጅን ብጠና ግን ተራራዎች መልስን ሰጡኝ በዝምታቸው ሚስጥሩ ገባኝ እነርሱም እርዳታ እንደሚያሻቸው ከታራራውም ላይ አሻቅቤ ሳይ በላይ በሠማይ ረድኤቴ መጣ እይተራመደ በደመናት ላይ እንደ እግዚአብሔር ያለ ማንም እንደሌለ ይህንን ስላየሁ የዘለዓለም አምላክ መኖሪያዬ አድርጌዋለሁ (2x) እንደተፈታች ሚዳቋ እንደተፈታች እንደተፈታች እምቦሳ እንደተፈታች ልውጣ ላይ ልውረድ ታች ነፍሴ ሃሴት ስላረገች ቧረቀች ፈነደቀች ነፍሴ ሃሴት ስላረገች (2x) እስቲ ክበር በሉት ክበር እስቲ ንገሥ በሉት ንገሥ ጌታን ክበር በሉት ክበር ጌታን ንገሥ በሉት ንገሥ እጅግ ደስ ይለኛል ሥሙ ሲወደስ ይንገሥ ይንገሥ ይንገሥ (2x) ይንገሥ ይንገሥ ይንገሥ ክበር ክበር ክበር ንገሥ ንገሥ ንገሥ ይክበር ይክበር ይክበር ይንገሥ ይንገሥ ይንገሥ በእኔና በሞት መካከል አንድ እርምጃ ቀርቶ እርሷንም ተራምዶ ውጦ ሊያስቀረኝ እጅጉን ጓግቶ በጠላትም ሰፈር በቃ ሽንፈቴ ተረጋገጠ ግን ረዳቴ መጣ በቅጽበት ነገሩ ተገለበጠ ሊሰለጥንብኝ ባለው ቀን ጠላቴ ሰለጠንኩበት ለእኔ በቆፈረው ጉድጓድ እርሱ ተቀበረበት ድል አድራጊው ጌታ ድል እያደረገ በሰልፉ መሃል በምሥጋና ነዶ በምርኮ ብዛት ያዘምረኛል/ያዘልለኛል (2x) እንደተፈታች ሚዳቋ እንደተፈታች እንደተፈታች እምቦሳ እንደተፈታች ልውጣ ላይ ልውረድ ታች ነፍሴ ሃሴት ስላረገች ቧረቀች ፈነደቀች ነፍሴ ሃሴት ስላረገች (2x) እስቲ ክበር በሉት ክበር እስቲ ንገሥ በሉት ንገሥ ጌታን ክበር በሉት ክበር ጌታን ንገሥ በሉት ንገሥ እጅግ ደስ ይለኛል ሥሙ ሲወደስ ይንገሥ ይንገሥ ይንገሥ (2x) ይንገሥ ይንገሥ ይንገሥ (3x) ንገሥ ንገሥ ንገሥ ይክበር ይክበር ይክበር ይንገሥ ይንገሥ ይንገሥ
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection