ከማንም ጋር አላወዳድርህም ከማንም ጋር እኩያ አላደርግህም (2x) ለጌታዎቹ ጌታ ነህ ለነገሥታቱም ንጉሥ ነህ ለኃያላኑም ኃያል ነህ እግዚአብሔር ልዩ ነህ ከዘለዓለም ዘለዓለም በፊት ብቻህን የነበርከው ከዘለዓለም ዘለዓለም በኋላ ብቻህን የምትኖረው ፍጥረት ቢያመልክ ባያመልክህ ቢዘል ባይሰግድልህ ከክብርህ ቅንጣት አይቀንስም እንኳንስ ሊያጐድልብህ ቅንጣት አይቀንስም እንኳንስ ሊያጐድልብህ (2x) እውነት ነው እኔ ዝም ብል ድንጋዮች ይናገሩልሃል እጅ እግሬን አጥፌ ብቀመጥ ኮረብቶች ይዘሉልሃል ወንዞች ያጨበጭቡልሃል አእዋፋት ይዘምሩልሃል ስለጐደለህ አይደለም እኔ የምጨምረው ስላነሰህም አይደለም እኔ የማበዛው ስለሚገባህና ስለተገባህ ነው (2x) የተለየ ነው አምላክነት ንግስናህ የተለየ ነው ገናናነትህ ዝናህ የተለየ ነው መቀመጫህ ዙፋንህ የተለየ ነው ማስፈራቱ የክብርህ አልፋ ነህ ኦሜጋ መጀመሪያ መጨረሻ አልፋ ነህ (አልፋ ነህ) ኦሜጋ (ኦሜጋ) መጀመሪያ (መጀመሪያ) መጨረሻ (መጨረሻ) አልፋ ነህ ኦሜጋ መጀመሪያ መጨረሻ አልፋ ነህ (አልፋ ነህ አልፋ ነህ) ኦሜጋ (ኦሜጋ ኦሜጋ) መጀመሪያ (መጀመሪያ መጀመሪያ) መጨረሻ (መጨረሻ) አልፋ ኦሜጋ ኦሜጋ ነህ መጨረሻ ሁሉን የምትገዛ ጌታ