Song Lyrics

በመጀመሪያ ላመስግንህ

Samuel Tesfamichael
Yemigermegn Medane New
አዝ፦ በመጀመሪያ ላመስግንህ ስለምን በሌላ ልጀምር በመሃከልም ልጨማምርበት ስለምን በሌላ ልቀጥል በመጨረሻ መደምደሚያዬ አምልኮ ይኸው ለአንተ ጌታዬ በመጨረሻ በመቋጫዬ ዝማሬ ይኸው ለአንተ ጌታዬ (2x) ያረክልኝ ነገር በዝቶ ስለምን ፊትህ ላጉረምርም አፌን በምሥጋና ልክፈት ማዘን በእኔ ላይ አያምርም ይኸው ምሥጋና ይኸው ዝማሬ አቀርባለሁ ዛሬ ይኸው ዕልልታ ይኸው ስግደቴ ለመድሃኒቴ አዝ፦ በመጀመሪያ ላመስግንህ ስለምን በሌላ ልጀምር በመሃከልም ልጨማምርበት ስለምን በሌላ ልቀጥል በመጨረሻ መደምደሚያዬ አምልኮ ይኸው ለአንተ ጌታዬ በመጨረሻ በመቋጫዬ ዝማሬ ይኸው ለአንተ ጌታዬ (2x) ብዙ ነገር አርገህልኝ ጥቂቱን ብትከለክለኝ ያውም ለጥቅሜ ብለህ እንጂ መች ለጉዳት አሰብክብኝ በግማሽ ልቤ ምሥጋና አልሰጥም እኔ አልዘምርም ገብቶኛል የአንተ የአምላኬ አላማ ይኸው ምሥጋና አዝ፦ በመጀመሪያ ላመስግንህ ስለምን በሌላ ልጀምር በመሃከልም ልጨማምርበት ስለምን በሌላ ልቀጥል በመጨረሻ መደምደሚያዬ አምልኮ ይኸው ለአንተ ጌታዬ በመጨረሻ በመቋጫዬ ዝማሬ ይኸው ለአንተ ጌታዬ (2x) አፌን ስከፍት በምሥጋና ሳቀርብ ለጌታ ሲሰጠኝ ማጉረምረም ማዘን መቆዘም አላገኙኝም ፈልገው ለቀው ይጠፉ ብቻዬን ቀረሁ ሰላም አገኘሁ ገና ያጡኛል ሳቀርብ ምሥጋና ላብዛ እንደገና አዝ፦ በመጀመሪያ ላመስግንህ ስለምን በሌላ ልጀምር በመሃከልም ልጨማምርበት ስለምን በሌላ ልቀጥል በመጨረሻ መደምደሚያዬ አምልኮ ይኸው ለአንተ ጌታዬ በመጨረሻ በመቋጫዬ ዝማሬ ይኸው ለአንተ ጌታዬ (2x)
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection