የጌቶች ጌታ ነው ኢየሱስ የማመልከው (3x) አታልቅስ ብሎ ከሃዘኔ ያጽናናኝ ከጐኔ ቆሞ ያበረታኝ (2x) መጽሃፉን ወስዶ ማኅተሙን የፈታ የነገሥታት ንጉሥ የጌቶቹ ጌታ ከይሁዳ ነገድ የሆነው አንበሳ ገናናው/ኃይለኛው ኢየሱስ ብቻውን ድል ነሳ (2x) ብቻውን ድል ነሳ አዎ ቻውን ድል ነሳ (2x) ኢየሱስ ድል ነሳ አሜን ኢየሱስ ድል ነሳ (2x) መለከት ይነፋ ይወራለት ዝናው አዋጁም ይታወጅ እንዳይኖር ያልሰማ ሞት መውጊያው ተሰብሮ ጉልበቱ ደቀቀ ሲኦል ተሸነፈ ቁልፉ ተነጠቀ ይህን ማድረግ የቻለ ከኢየሱስ ሌላ ማነው አያንስበትም ወይ ታድያ ከዚህ በላይ ባመልከው ይህን ላደረገው አምልኮ ይብዛለት ይህን ላደረገው ክብር ይጨመርለት ይህን ላደረገው ይድመቅ ዕልልታው ይህን ላደረገው ስለሚገባው አምልኮ ይብዛለት ክብር ይጨመርለት ይድመቅ ዕልልታው ስለሚገባው (4x) የጌቶች ጌታ ነው ኢየሱስ የማመልከው (3x) አታልቅስ ብሎ ከሃዘኔ ያጽናናኝ ከጐኔ ቆሞ ያበረታኝ (2x) መጽሃፉን ወስዶ ማኅተሙን የፈታ የነገሥታት ንጉሥ የጌቶቹ ጌታ ከይሁዳ ነገድ የሆነው አንበሳ ገናናው/ኃይለኛው ኢየሱስ ብቻውን ድል ነሳ (2x) ብቻውን ድል ነሳ አዎ ቻውን ድል ነሳ (2x) ኢየሱስ ድል ነሳ አሜን ኢየሱስ ድል ነሳ (2x) ጌታዎች ባርያዎች ድሆች ባለጸጋዎች ታናናሽ ታላላቅ ሃያላን ደካሞች ጉልበት ሁሉ ለእርሱ የሚምበረከክለት ሕያውም ግዑዙም የሚንቀጠቀጥለት እረ እንዴት ምስጉን ነው ወዶ የሚያመልከው በዕልልታ በሆታ ስሙን ያወደሰው ይህን ላደረገው አምልኮ ይብዛለት ይህን ላደረገው ክብር ይጨመርለት ይህን ላደረገው ይድመቅ ዕልልታው ይህን ላደረገው ስለሚገባው አምልኮ ይብዛለት ክብር ይጨመርለት ይድመቅ ዕልልታው ስለሚገባው (4x)