አባቶች በእምነት አምልከውት አለፉ ነቢያት አወሩለት መለከትን ነፉ ሓዋሪያት የሰሙት በዐይናቸው ያዩት በእጆቻችሀው ዳሰው የመሰከሩለት መቃብር ፈንቅሎ ሞትን ድል የነሳው እርሱን በማምለኬ እኔ እንጓደዳለሁ ከሰማያት በላይ ከፍ ብሎ ያለ በዘምናት መሃል እጅግ የከበረ በሃይል በችሎቱ ዝናው የገነነ በፍጥረት ሁሉ ላይ የተመሰገነ ይሄ ነው ጌታ ይሄ ነው ይሄ ነው አምላክ ይሄ ነው (2x) እኔ የማመልከው አዝ፦ የማመልከው ይህ የእኔ ጌታ የማደንቀው የምሰግድለት እርሱ ብቻ የአማልክት አምላክ የማመልከው ይህ የእኔ ጌታ የማደንቀው የምሰግድለት እግዚአብሔር የአማልክት አምላክ ፀሐይን አቁሞ ጨረቃን ያዘገየ አሰራሩ ልዩ ከሁሉ የተለየ ባሕርን እንደግድግዳ እንደክምር ያደረገው የጥንቱ እግዚአብሔር ዛሬም እግዚአብሔር ነው ይሄ ነው ጌታ ይሄ ነው አምላክስ ካሉ እንዲህ ነው መኖር ካልቀረ እርሱ ነው ካመለኩ አይቀር እርሱን ነው አዝ፦ የማመልከው ይህ የእኔ ጌታ የማደንቀው የምሰግድለት እርሱ ብቻ የአማልክት አምላክ (2x) የአህዛብ አማልክት ጣኦታቶች ናቸው አይሰሙ አያዩ ቢጠሩ አይሰሟቸው አምላካቸው ይቀስቀስ ተኝቷል ወይ ሲባል እኔ የማመልከው በእሳት ይመልሳል የተነሱበትን ሁሉ ያደቀቀ በአሸናፊነቱ ግድሉ የታወቀ ይሄ ነው ጌታ ይሄ ነው አምላክስ ካሉ እንዲህ ነው መኖር ካልቀረ እርሱ ነው ካመለኩ አይቀር እርሱን ነው አዝ፦ የማመልከው ይህ የእኔ ጌታ የማደንቀው የምሰግድለት እርሱ ብቻ የአማልክት አምላክ (2x)