ክፉ ሳይመጣ ከሩቅ አይተህ ለልጅህ ሚስጥርን ትገልጣለህ እንዳልጠፋ በንፋስ ማዕበሉ ትታደገዋለህ ሆነህ መርከቡን አዋቂ ነህ ሁሉንም አውቀኸዋል የጥፋትን ውኃ ሰብስበሃል የሞገዱን መናወጥ ዝም አሰኘህ ለባሪያህ መልካምን አደረግህ ብዙ ጐርፍ ተነስቶ ሕይወቴን ሊያጠፋ ዕንቁዬን ሊያስጥለኝ ሊያስቆርጠኝ ተስፋ ነፍሴን ያስጨነቀ ያናወጠ መከራ ቀስ በቀስ እየገፋ አወጣኝ ወደ ተራራ በእሳት ካልነጠረ ወርቅ እንደማይደምቀው ያኔ እያስጨነቀኝ ለካ ለበጐ ነው ያረጀው የደከመው እምነቴ በፀጋህ ታድሶ በዝማሬ ተተካ የትላንቱ ለቅሶ ሃሌሉያ (3x) ለታመነህ ሆነሀዋል መጠለያ የተመካብህ አመለጠ በአንተ ጉያ ሃሌሉያ (3x) የታመነህ ስንቱ ዳነ በአንተ ጉያ የተመካብህ ስንቱ ዳነ በአንተ ጉያ የታመነ አመለጠ በአንተ ጉያ