ገመድ በአንገቴ ሳይገባ እጅም ሰንሰለት ሳያስረው እግሬ እየዘለለ አየተወራጨሁ ታዲያ የምን እስራት ነው ታዲያ የምን እስራት ነው አዝ፦ ጌታ ሆይ ስውር እስሬን አሳየኝ እንዳልራመድ ያደረገኝ አሳየኝ ጌታ ሆይ ስውር እስሬን አሳየኝ እንዳልራመድ ያደረገኝ አሳየኝ ዓይኔ እያየ በሚያልፈው ላይ እንዳልዘረጋ እጄን መዘዙን ሳላይ (እባክህ እርዳኝ) እንድጋልብበት ሲያምረኝ ፈረሱ ልጓም ከሌለው ይቅርብኝ እርሱ (2x) አዝ፦ ጌታ ሆይ ስውር እስሬን አሳየኝ እንዳልራመድ ያደረገኝ አሳየኝ ጌታ ሆይ ስውር እስሬን አሳየኝ እንዳልራመድ ያደረገኝ አሳየኝ ከንጉሥ ገበታ ከቃሉም ማዕድ ሁሌም ማልጠፋ ሆኜ የንጉሥ ልጅ ምነው መክሳቴ ምነው መመንመኔ የዓለም ቤዛ ሆነኀኝ መድህኔ (2x) ገመድ ከአንገቴ ሸክም ከጫንቃዬ ይሰበር የእግር ብረቱ ይቆረጥ ከእጄ ሰንሰለቱ ፍታልኝ እባክህ ፍታልኝ ፍታልኝ እስሬን ፍታልኝ ፍታልኝ እባክህ ፍታልኝ ፍታልኝ ውዴ ፍታልኝ (2x) ፍታልኝ ፍታልኝ ኢየሱስ እስሬን ፍታልኝ አባቴ አባቴ ፍታልኝ ፍታልኝ