የከበረ ከሁሉ የተሻለ የከበረ ከሁሉ የተሻለ ሰውነቴ ለአንተ አቀርባለሁ (2x) እኔነቴን ለአንተ አቀርባለሁ (2x) መሰዊያን ሰራሁ ልሰዋልህ በፊትህ ላቀርበው ያለኝን በሙሉ ታውቀዋለህ የቱን ነው ምትሻው እያልኩኝ ስደረድር ምድርና ሞላዋ ለካስ የአንተ ነው የሚቃጠል መስዋዕት ደስ እንዳያሰኝህ ይህንን ተረዳሁ ታዲያ እኔም ምኔን ልስጥህ ምን ሰጥቼ/ሰውቼ ደስ ላሰኝህ እያልኩኝ ስጠይቅ ቃልህን ስጠው/ሰዋው አለኝ እራስህን (2x) ስለዚህ እራሴን ሕያውና ቅዱስ አድርጌ ፊትህን ደስ እንዳሰኘሁ ፈቀድኩኝ ልሰዋ ይኸው ልዩ ጣዕም የመዓዛ ሽታ ሆኜ ልቅረብ በፊትህ ዕይታ ከሚቃጠል መስዋዕት ጋራ ወደፊትህ እመጣለሁ የአምልኮዬ መዓዛ ሽታ ዙፋንህን ይክበበው በምህረት የተሞላህ ታላቅ አምላክ ነህና አሁንም አበዛለሁ ከነፍሴ ምሥጋና ኦ በምሥጋና በዝማሬ እመጣለሁ ኦሆሆ ወደ ማደሪያህ እገባለሁ (6x)