አንተ የእኔ ነህ/2 ማንም የማይወስድህ አለኝ የምለው የራሴ እርግጠኛ የምሆነው በመንፈሴ አንተን ብቻ አንተን ብቻ ነው የራሴ የግሌ የምለው እርግጠኛ እርግጠኛ ነኝ/3 እኔን ካንተ ማንም እንዳይለየኝ ሃብት ወዳጅ ከእኔ ጋር ያሉ በምድር ላይ እዚሁ ይቀራሉ ለዘላለም ያገኘሁህ ሃብቴ መንፈስ ቅዱስ ህይወቴ ነህ ርስቴ እርግጠኛ እርግጠኛ ነኝ/3 እኔን ካንተ ማንም እንዳይለየኝ የማላይህ የማልዳስስህ ከማየው በላይ ግን ደግሞ የማምንህ ከእስትንፋሴ ይልቅ ቅርብ ነህ መንፈስ ቅዱስ የልቤ ወዳጅ ነህ እርግጠኛ እርግጠኛ ነኝ/3 እኔን ካንተ ማንም እንዳይለየኝ