Song Lyrics

ኢየሱስ ድል ነሳ

የጌቶች ጌታ ነው ኢየሱስ የማመልከው መፅሃፉን ወስዶ ማህተሙን የፈታ የነገስታት ንጉስ የጌቶቹ ጌታ ከይሁዳ ነገድ የሆነው አንበሳ ገናናው ኢየሱስ ብቻውን ድል ነሳ ከእርሱ ጋራ ሊሰለፉ የወደዱ ሁሉ አለፉ ኢየሱስ ግን አለ በዙፋኑ በማእረጉ በስልጣኑ የለም የለም እንደርሱ ያለ የለም በሰማይ የለም በምድር የለም/2 የከፈተውን ማን ይዘጋዋል የዘጋውን ማን ይከፍተዋል ተውባይ ከልካይ አንድ እንኩዋን የሌለው ቁልፉ እሱ እጅ ብቻ ነው ከዘላለም እስከ ዘላለም ህያው ሆኖ የሚኖር እንደርሱ የለም ከነገድ ከቁዋንቁ ህዝቡን የዋጀው የታርደው በግ እርሱ ብቻ ነው
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection