አንተ ብቻነህ ፈጣሪ ብቻህን ፈጣሪ ጀማሪ ፈጣሪ የሁሉ ፈጣሪ ይሁን ይሁን ብለህ ፍጥረታትን በቃልህ ፈጠርህ መጥቶልሃል ያልነበረው አቤት ብሎሃል የማይሰማው አንተ ያልከው የቀረ የለም ፀንቶልሃል በቃልህ ሁሉም የሰማይ ምድሩ የውቅያኖሱ የሚበሩ ሚንቀሳቀሱ ፈጥረህ ብቻ መቼ ተውካቸው መልካም ነው ብለህ ባርካቸው የህያዋን ምንጭ ህይወት ጀማሪ የግኡዛን ደግሞ ፈጣሪ ማን ነበረና ሊያማክርህ አንተ ብቻህን ሁሉን ፈጣሪ ያላማካሪ ብቻህን ሰሪ እግዚአብሔር ነህ ሁሉን ፈጣሪ