ነፋሱ ቢነፍስ ወጀቡ ቢያጉዋራ በበዛው ሰላምህ አለህ ከኔ ጋራ አለም ብትናወት ማእበሉ ቢበዛ ነፍሴ እርፍ አለች በፍቅርህ ተይዛ የዘላለሜ ነህ ሁሉ ሲቀር ኃላ መልህቅ የሆንከኝ ግራ እንዳልጋባ መልህቄ/2x/ ያዝከኝ ኢየሱሴ የፍቅርህ ሰንሰለት አጥብቆ ይዞኛል እኔ ብደክምበት መቼ ይተወኛል በሞትህ ወደ ታች ወርደህ መልህቄ ያዝከኝ ልዩ ፍጥረት ቢሆን ሞትም እንዳይለኝ እንደ ነፍስ መልህቅ በሆነ ተስፋ እርግጥ እና ፅኑ መቼም የማይጠፋ በዚህኛው ቢሆን በወዲያኛው አለም ጥብቅ አርገህ ያዝከኝ እስከለዘላለም አምናለው ዛሬም በዚህ አለህ አምናለው ዛሬም ትሰራለህ