Song Lyrics

ክንዳቹ አይላላ

ክንዳችሁ አይላላ ጉልበታችሁ አይበላ የእስራኤል አምላክ አለ ከእኛ ጋራ የናዝሬቱ ኢየሱስ አለ ከእኛ ጋራ ከግብፅ ከባርነት ከፈርዖን ብዛት ህዝቡን ያሳረፈ ከጭንቀት ከፍርሃት በእሳት በደመና በቀን ሌት የመራ ያው የእስራኤል አምላክ አለ ከእኛ ጋራ መንገዱ እጅግ እሩቅ ቢመስል ሚከብድ ማያልቅ የአለም ኑሮ ፈተና ቢሆንም ትንቅንቅ ከእኛ ጋራ ያለው አለምን አሸንፏል እስከ ፅዮን ድረስ በድል ይመራናል ክንዳችሁ አይላላ ጉልበታችሁ አይበላ የእስራኤል አምላክ አለ ከእኛ ጋራ አማኑኤል እርሱ አለ ከእኛ ጋራ ከእግዚአብሔር ጋር ሆነው የወጡ ወደ ሰልፉ የአንበሶችን አፍ ዘጉ የእሳትን ሃይል አጠፉ በቅንም ፈረዱ መንግስታቱን ድል ነሱ አለምን ኮነኑ ጣኦትን አፈረሱ ዛሬም ከበውናል እነርሱ እንደደመና ክንዳችን እንዳይላላ ጉልበታችን ይፅና የፃድቅ ጉልበቱ ነውና እምነቱ ቅዱሳን ካህናቱ እልፍ በሉ በርቱ ክንዳችሁ አይላላ ጉልበታችሁ አይበላ የእስራኤል አምላክ አለ ከእኛ ጋራ ተስፋውን የሰጠው አለ ከእኛ ጋራ ሃይልን በሚሰጠን ሁሉን እንችላለን በወደደን በእርሱ ከአሸናፊዎች እንበልጣለን ክንዳችን ይበርታ ጉልበታችን ይፅና አምላካችን ብርቱ ሁሉን ቻይ ነውና
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection