Song Lyrics

እታመናለሁ

የታመነህ ሰው እንደንጋት ብርሃን ህይወቱ ይደምቃል የታመነህ ሰው ሙሉ ቀን እኪሆን ጨምሮ ያበራል አንተን ያመነ አይፈራ አይደነግጥ በለሊቱ አንተን ያመነ ቃልህ ይሆንለታል ለእግሩ መብራቱ የሚጤሰውን ጥዋፍ አታጠፋምና ቅጥቅጡን ሸንበቆ አትሰብርምና ስለዚህ አይኔን ወዳንተ ላቅና ስለዚህ ልቤን ባንተ ላፅና አይኔን አቀናለሁ ልቤን አፀናለሁ አንተኑ/2 እታመንሃለው አንተኑ/2 እደገፍሃለው እግዚአብሔር አለቴ እታመንሃለው አምባ መድሃኒቴ እደገፍሃለው የታመነህ ሰው በወንዝ ዳር እንዳለ ዛፍ ይሆናል የታመነህ ሰው ሁሌ ይለመልማል ሁሌም ያፈራል አንተን ያመነ ዙሪያው ደረቅ ቢሆን ምድረበዳ አንተን ያመነ ለሌላው ይተርፋል አይሆንም ባለ እዳ የታመነህ ሰው ቃልህን ይሰማል ደግሞም ያደርጋል የታመነህ ሰው በፀናው አለት ላይ ቤቱን ይሰራል አንተን ያመነ ዝናብ ጎርፍ ንፋሱ መጥቶ ቢገፋው አንተን ያመነ አልፎት ይሄዳል እንጂ ጫፉን አይነካው
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection