በእኔ ፈንታ ተተክቶ ወጥቻለው እስሬ ተፈቶ በሃጥያቴ ምክንያት እንዳልቀጣ ክርስቶስ ኢየሱስ ክብሩን ትቶ መጣ እዳዬንም እሱ ከፍሎልኛል ነፃ ሰው ነኝ ዋሴ ሆኖልኛል አድራሻዬ በሰማዩ ስፍራ አድርጎታል ከእግዚአብሔር ጋራ ኩነኔ የለብኝም አሁን ኩነኔ ነፃ ወጥቻለው በመድህኔ ምንም ሳላደርግ ምንም ሳልስራ በአብ ቀኝ ተቀመጥኩ ከእየሱሴ ጋራ ምንም ሳልከፍል ያለምንም ዋጋ የዘላለም ህይወት አገኘው በፀጋ እንዲሁ በፀጋ/2 የዘላለም ህይወት አገኘው በፀጋ ራሱ ሰጠ ለኔ ሊገረፍ አንድም ጅራፍ በኔ ላይ እንዳያርፍ መራራውን ፅዋ እንዳልጠጣው አበሳዬ ወስዶ ጨረሰው የአለምን ሃጥያት ሚያስወግደው የእግዚአብሔር በግ በደሌን ሰቀለው በራሱ ደም ይዞኝ አብ ጋር ገባ አለበሰኝ ፀጋውን እንደ ካባ