Song Lyrics

እድለኛ

አንተ ባለህበት በከበረው ስፍራ ካንተ ጋራ ልኖር ስምህን እንድጠራ እድሉን አገኘው በቤትህ ልቀድስ እጥፍ ልስገድልህ ነፍሴን ፊትህ ላፍስስ እንዴት መታደል ነው ስምህን መጥራቱ ኢየሱስ ኢየሱስ ኢየሱስ ማለቱ የተመረጠ ስም ከስም ሁሉ በላይ አይኔን አድርጎታል ካንተ ሌላ እንዳላይ የህይወቴ ኢየሱስ ጌታ ነህ ኢየሱስ የኑሮዬ ኢየሱስ ንጉስ ነህ ኢየሱስ መአዛህን ኢየሱስ ስወደው ኢየሱስ መገኘትህ ኢየሱስ ህይወቴ ነው ኢየሱስ ኢየሱስ ወደድኩህ ከእልፍ ከአእላፋት መረጥኩህ ውዴ ከእንቁ ትበልጣለህ ከማር ወለላ ትጣፍጣለህ እረ እንዴት እድለኛ ነኝ በፊትህ ሞገስን አገኘሁኝ የኔ ብቻ አይበቃም ዝማሬ ይገዛልህ ዘር ማንዘሬ የቤትህ ስርአት በሚደረግበት ህዝቡም መላእክቱም ቅዱስ በሚሉበት እድሉን አገኘው ዘላለም ላመልክህ ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ እያልኩ ከቅዱሳንህ እንዴት መታደል ነው ዘላለም ማምለኬ ጎንበስ ቀና እያልኩ ፊትህ ተንበርክኬ በማይነገር ክብር በሚደነቅ ብርሃን ላይህ ጉዋጉቻለው ውዴ ኢየሱስ አንተን ኢየሱስ ሙሽራዬ ኢየሱስ ቶሎ ና ኢየሱስ መናፈቄ ኢየሱስ በዝትዋልና ኢየሱስ ማዶ ማዶ ኢየሱስ ማዶ እያየው ኢየሱስ አማትሬ ኢየሱስ እጠብቅሃለው
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection