Song Lyrics

ትለያለህ

የክብር ንጉስ ሆይ እንዴት ታላቅ ነህ ከዙፋንህ ስር በእውነት በመንፈስ ልስገድልህ ከሰው ልጆች ይልቅ ያማረ ውበትህ የፀጋ ቃል ሁሌ ያፈሳል ከንፈርህ አይኖቼ አይተውህ ፈዘዙ በክብርህ /2 ማን ሊመስልህ አረ ማን ሊያክልህ አንተ እኮ ከአማልክት ትለያለህ ውዴ ከአእላፋት ትበልጣለህ ፊትህ እንደ ፀሃይ በሃይል ያበራል እንደ ብዙ ውሆች ድምፅህም ያስፈራል በግርማህ ተገርሜ ቀረሁኝ ተደምሜ ማን ሊመስልህ አረ ማን ሊያክልህ አንተ እኮ ከአማልክት ትለያለህ ውዴ ከአእላፋት ትበልጣለህ ሃሌሉያ/8
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection