Song Lyrics

ይወራ ዝናው

ዝናውን ለሰማው እጅግ ያስፈራል ባለዝና እንደሱ ከየት ይገኛል በዘመናት መሃል ይታወቃል ብቻውን የበላይ ሆኖ ይኖራል እግዚአብሔር /8/ እግዚአብሔርን ከኔ ጋራ ታላቅ አርጉት ዝናው ይወራ /8/ ይወራ ዝናው ይወራ/2/ በምድር ሁሉ ይወራ ይወራ ዝናው ይወራ/2/ በዓለም ሁሉ ይወራ ይወራ ዝናው ይወራ አንጎዳጎደ ልዑል ቃሉን ሰጠ በክብሩ ሲቆም ምድርን አናወጠ የዘላለም ተራሮች ተፈረካከሱ የጥንትም ኮረብቶች ወዲያው ፈራረሱ ከሚንቦገቦገው ጸዳል የተነሳ ፍላጾች ከወጡበት ብርሃን የተነሳ ጨረቃና ጸሐይ በቦታቸው ቆሙ በክብሩ ነጸብራቅ አየተደመሙ እየተደመሙ እየተደመሙ በክብሩ ነጸብራቅ አየተደመሙ/2/ እግዚአብሔር /8/ ክብሩ ሰማያትን ሁሉ የሸፈነ ስሙም በምድር የተመሰገነ ለታላቅነቱ ፍጻሜ የሌለው በዘመናት መሃል እርጅና ማያውቀው ከዋክብት ታዘዙ በህዋ አበሩ በአፍንጫው እስትንፋስ ውሆች ተከመሩ ትልቅ የሚለው ቃል ፍጹም የማይገልጸው እጅጉን ያስፈራል ዝናውን ለሰማው ዝናውን ለሰማው ዝናውን ለሰማው/2/ እግዚአብሔር /8/
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection