Song Lyrics

ግልሙትናዋ

Samuel Tesfamichael
Girma Mogesih
ግልሙትናዋ እጅግ ስለበዛ ሥራዋ አይቆምም ጻዲቅ ካልተነሳ የነብያትና የቅዱሳን ጠላት ጻድቅ ታጥቀህ ውጣ እርሱዋን ተበቀላት ኤልዛቤል ትዋረዳለች ኤልዛቤል ውሾች ይበሏታል ኤልዛቤል ትዋረዳለች ኤልዛቤል ሥራዋ ይፈርሳል [1] ጻዲቁ ሄደ ገሠገሰ (4x) በዚህ ዘመን ሕዝቡን ያራደ ያንቀጠቀጠ እሱ ማን ነው (3x) የእግዚአብሔር የእቃ ጦር ለብሶ ጻድቅ ይጋጠመው (3x) ጻዲቁ ሄደ ገሠገሰ (4x) ጉልበት ሆኖለታል እግዚአብሔር አምላኩ በእምነት እሮጠ እየያ ፊት ፊቱ አልተመለሰም ከቶ ወደ ኋላ ተስፋው አምላኩ ነው አያይም ሌላ (2x) በልዑል አምላክ ሥም ተማምኖ በትከሻው መሃል አድሮ ቅድስና ለእግዚአብሔር ብሎ ይኖራል ጌታውን አክብሮ ጻዲቁ ሄደ ገሠገሰ (4x) የእግዚአብሔር ዓይኖች ያረፉበትን ሰው ባዶ የምታደርግ የምታስቀር ላጭታው አልያዝም የሚል ደግሞ የጨከነ እርሷን የሚያዋርድ ጻድቅ ወዴት አለ ደሊላ ትዋረዳለች ደሊላ ጌታ ይበቀላታል ደሊላ ትዋረዳለች ደሊላ ሥራዋ ይፈርሳል ደሙ በግንባሩ ሆኖ በመቃኑ እንዳይነካ እምላክ ከእርሱ ጋራ ነው ለካ (2x) ጻዲቁ ሄደ ገሠገሰ (4x)
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection