Song Lyrics

በሰማይ በምድር

Samuel Tesfamichael
Girma Mogesih
በሰማይ በምድር የከበርከው ከጥንትም ጀምሮ የነበርከው (2x) ዙፋንህ ከፍ ያለ የፀና እግዚአብሔር ብቻህን ገናና (3x) ገናና ብቻህን ገናና ገናና ብቻህን ነህ ገናና ለሁሉም ምዕራፍ መጀመሪያቸው መውጣትና መግባት ሁሉ በእጅህ ነው ባለዝና ነህ ሁሉም ያውቅሃል ገናናነትህ ደግሞ ዓለምን ሞልቷል የከበረ የነገስህ ከፍ ያልህ የበረታህ እግዚአብሔር ብቻ ጌታ ነህ (2x) አምላኬ ብቻ ጌታ ነህ (2x) በሰማይ በምድር የከበርከው ከጥንትም ጀምሮ የነበርከው (2x) ዙፋንህ ከፍ ያለ የፀና እግዚአብሔር ብቻህን ገናና ( ገናና ብቻህን ገናና ገናና ብቻህን ነህ ገናና አማልክት ተብለው እጅግ ተፈርተው የሰዎች ሥራዋች ፍጡር ፈጥሩዋችው አይሰሙ አያዩ ደግሞ አይመልሱ ላወዳድርህ ነው ወይ አንተን ከእነሱ ከእንግዲህ በእኔ ዘር ከኔ በኋላ አይመለክም ካንተ ሌላ አይመለክም ካንተ ሌላ (2x) ወደር የሌለህ አቻ የሌለህ መሳይ የሌለህ አቻ የሌለህ (2x) ሰማይ ተቀምጠህ ምድር የምትረግጥ ትላንት ዛሬ ነገ የማትለወጥ እረግምና ከፍ ያለ ዙፋንህ የማይቆጠር ነው እድሜ ዘመንህ ከእንግዲህ በእኔ ዘር ከኔ በኋላ አይሰበክም ካንተ ሌላ (2x) ከእንግዲህ በእኔ ዘር ከኔ በኋላ አይለመንም ካንተ ሌላ (2x) ሌላ አይለመንም ካንተ ሌላ ሌላ ሌላ አይለመንም ካንተ ሌላ ሌላ ከብሮ አይታይም ካንተ ሌላ ሌላ ሌላ ነግሶ አይታይም ካንተ ሌላ ወደር የሌለህ አቻ የሌለህ መሳይ የሌለህ አቻ የሌለህ (2x)
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection