Song Lyrics

ምስክር ነኝ

Samuel Tesfamichael
Girma Mogesih
አዝ፦ ምስክር ነኝ እኔ አምላክ እንደሆንክ ምስክር ነኝ እኔ ጌታ እንደሆንክ እመሰክራለሁ እንደምትረዳ ምስክር ነኝ እኔ እንደምትደርስ ለተጐዳ እኔን ያዩ ዓይኖችህ ይባረኩ ለዘላለም እኔን የሰሙ ጆሮዋችህ ይባረኩ ለዘላለም እኔን ያነሱ እጆችህ ይባረኩ ለዘላለም እኔን ያጽናኑ ቃሎችህ ይባረኩ ለዘላለም በሰማይ ተቀምጠህ ከፍ ባለ ስፍራ በምድር ሆኜ ትንሽ ሰው እርዳኝ ብዬ ስጣራ ሰምተህ ከመለስከኝ ቀኝህ ከረዳችኝ ላመስግን በዘመኔ ክንድህ ካገዘችኝ ኦሆ ክንድህ ካገዘችኝ አዝ፦ ምስክር ነኝ እኔ አምላክ እንደሆንክ ምስክር ነኝ እኔ ጌታ እንደሆንክ እመሰክራለሁ እንደምትረዳ ምስክር ነኝ እኔ እንደምትደርስ ለተጐዳ እኔን ያዩ ዓይኖችህ ይባረኩ ለዘላለም እኔን የሰሙ ጆሮዋችህ ይባረኩ ለዘላለም እኔን ያነሱ እጆችህ ይባረኩ ለዘላለም እኔን ያጽናኑ ቃሎችህ ይባረኩ ለዘላለም ዮርዳኖስ ሲከፈል ተዓምር ማሳያ ከመሃል ድንጋይ ወጣ ሆነ መታሰቢያ እኔም በዚህ ዘመን ሥራህን ስላየሁ ሕያው ለመሆንህ ምስክር እሆናለሁ ኦሆ ምስክር እሆናለሁ እንኳን ወዳጆቼ እዚህ መድረሴ እኔም ለእራሴ አስቤው አላውቅም በህልሜም በውኔ (2x) ጠላቶቼማ የኔን ውድቀት የሚሹ አሳፈርካቸዉ ታምራትህን አዩ (2x) በለቅሶ ተዘርቶ በደስታ ከታጨደ በኩርንችት ፈንታ ባርሰነት ከበቀለ ንጉሥ ለሚወደው ሰው እንዲህ ይደረጋል ማይጠፋ ምልክት ነው ዓይኔ ይህን አይቷል ኦሆ ዓይኔ ይህን አይቷል አዝ፦ ምስክር ነኝ እኔ አምላክ እንደሆንክ ምስክር ነኝ እኔ ጌታ እንደሆንክ እመሰክራለሁ እንደምትረዳ ምስክር ነኝ እኔ እንደምትደርስ ለተጐዳ እኔን ያዩ ዓይኖችህ ይባረኩ ለዘላለም እኔን የሰሙ ጆሮዋችህ ይባረኩ ለዘላለም እኔን ያነሱ እጆችህ ይባረኩ ለዘላለም እኔን ያጽናኑ ቃሎችህ ይባረኩ ለዘላለም እንኳን ወዳጆቼ እዚህ መድረሴ እኔም ለእራሴ አስቤው አላውቅም በህልሜም በውኔ (2x) ጠላቶቼማ የኔን ውድቀት የሚሹ አሳፈርካቸዉ ታምራትህን አዩ (2x)
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection