Song Lyrics

ሰማያት ያንጠባጠቡት

Samuel Tesfamichael
Girma Mogesih
ሰማያት ያንጠባጠቡት ዝናብ ቀላያትም የያዙት ውኃ የምድርን ዛፎች ባስተባብር በደን ያሉ በበረሃ አሃሃ ውኃው ቀለም ቢሆን አሃሃ ዛፉም ደግሞ ብዕር አሃሃ ሁለቱም ቢጣመሩ አሃሃ ክብርህን እንዲያወሩ አዝ፦ ብዕሬ እንኳን አንደበት ኖሮት ቢፈጠር ኧረ ስንቱን ስንቱን ይናገር ነበር (2x) ተራ ንጉስ ቤት እንኳን ገብቼ ስለእርሱና ዘሩ ቀለሜን በከንቱ ጨርሼ ንጉሥ ዘውዱን ሲደፋ የጻፍኩት አኔው ሰምቼ ሲሻር ሲዋረድ ተረኩት ደግሞ መልሼ አሃሃ ሰልችቶኛል ስተርከው የምድሩን አሃሃ ግራ ይገባኝ ሲሾሙና ሲሻሩ አሃሃ ምን አለ ሰዎች የላዩን ብትጽፉብኝ አሃሃ የምድሩን ከማውራት መተረክ ብትገላግሉኝ አሃሃ ጥሜ እንዲረካ የልቤ እንዲደርስ አሃሃ እጅግ ደስ ይለኛል ቀለሜን ስለእርሱ ብጨርስ አዝ፦ ብዕሬ እንኳን አንደበት ኖሮት ቢፈጠር ኧረ ስንቱን ስንቱን ይናገር ነበር (2x) ወዶ አፍቅሮ ሲያስብ ሰው በልቡ ይጠበብብኛል ለመግለፅ የውስጥ ሃሳቡ ወደድኩኝ ባለበት ቅፅበት ጠላሁ ደግሞ ይልብኛል ወረት ያለው ፍቅር ለእኔስ ግራ ገብቶኛል አሃሃ ሰልችቶኛል ስተርከው የምድሩን አሃሃ ግራ ይገባኛል ስዋደዱ ሲጣሉ አሃሃ ምን አለ ሰዎች የላዩን ብትጽፉብኝ አሃሃ የምድሩን ከማውራት መተረክ ብትገላግሉኘ አሃሃ ጥሜ እንዲረካ የልቤ እንዲደርስ አሃሃ እጅግ ደስ ይለኛል ቀለሜን ስለእርሱ ብጨርስ አዝ፦ ብዕሬ እንኳን አንደበት ኖሮት ቢፈጠር ኧረ ስንቱን ስንቱን ይናገር ነበር (2x) ከድሮ ጀምሮ ሁኔታው የማይቀየር እንዳለ የነበረ እንዲሁ ደግሞ የሚኖር ጥንት ስለእርሱ የጻፍኩት ያው ነው አልቀየርኩት ከትውልድ ትውልድ ይሄው አሳለፍኩት አሃሃ ስለመለወጡ ሁሌ የማልሰጋበት አሃሃ ከሁሉ የተለየ ጽናትን ያየሁበት አሃሃ ብጀምር ላወራ ስለእርሱ መስሎኝ አንደሰው አሃሃ ቀለሜ አለቀ እንጂ እሱንማ መች ልጨርሰው አሃሃ ብቀጥል ላወራ ስለእርሱ መስሎኝ እንደሰው አሃሃ አኔ አለኩ እንጂ ዘመኑን መች ልጨርሰው አዝ፦ ብዕሬ እንኳን አንደበት ኖሮት ቢፈጠር ኧረ ስንቱን ስንቱን ይናገር ነበር (2x)
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection