በጥበብህ በችሎታህ እንዳንተ ያለ ማነው ጌታ (2x) ዕውቀትህ የተለየ ፍጥረት እንዳንተ አልሰማ አላየ (2x) (አሃሃ) ትልቅ ነህ ብልህም (አሃሃ) ከዚያም ትልቃለህ (አሃሃ) ጌታዬ እግዚአብሔር (አሃሃ) በማን ልመስልህ ከምልህ በላይ ነህ የኔ ጌታ (4x) ሰው ከፍታ መጨረሻ መርገጫህ ነው ላንተ መነሻ (2x) ታች ብወርድ ላይ ቢወጣ የሚመስልህ አንድም ታጣ ታች ብወርድ ላይ ቢወጣ የሚያህልህ አንድም ታጣ (አሃሃ) ከህዝብህ ጋር ሆኜ (አሃሃ) ስምህን ባውድስ (አሃሃ) እንኳን ልጨርሰው (አሃሃ) ከመሃሉም እልደርስ ጥበብህ ብዙ ነው የኔ ጌታ (2x) ዕውቀትህ ሠፊ ነው የኔ ጌታ (2x) ገዢዎችን ትሾማለህ ሲያሻህ ደግሞ ታወርዳለህ ገዢዎችን ትሾማለህ ሲያሻህ ደግሞ ትሽራለህ ልዕልናህ እጅግ ከፍ ያለ ካንተ በላይ ማንም የለ (2x) (አሃሃ) ከህዝብህ ጋር ሆኜ (አሃሃ) ስምህን ባውድስ (አሃሃ) እንኳን ልጨርሰው (አሃሃ) ከመሃሉም እልደርስ ከምልህ በላይ ነህ የኔ ጌታ (2x) ልገልፅህ አልችልም የኔ ጌታ (2x) ላምልክ እንደገና አሃ (3x) አምላኬ ነህና ላንግሥ እንደገና አሃ (3x) ንጉሤ ነህና (2x)