Song Lyrics

ከጉባኤው መሃል

Samuel Tesfamichael
Girma Mogesih
ከጉባዔው መሃል ብዙ ሕዝብም ካለበት ተጋባዥ ሰው ሆኜ ያኔ በፍርሃት ህዝቡ ብዙ ግን ባንድ ድምፅ አቤት ዝማርያቸው መፅሐፍ ተከፍቶ ይነገራል ሰምቼ ማላውቀው (2x) ከቃሉ የህይወት ውሃ ወደልቤ ፈሰሰ ሳላቅማማ ጠጣሁት ውስጤም ረሰረስ ኧረ እንዴት ያለ ቀን ነው ዳግመኛ ተወለድኩኝ በልቤ አምኝ በአፌም መሰከርኩኝ በዚያን ቀን አሃሃ ታሪኬ ተቀየረ በዚያን ቀን ኦሆሆ ቀንበሬ ተሰበረ በዚያን ቀን ሽክሜም ቀለለልኝ በዚያን ቀን ኢየሱስ ጌታ ነው አልኩኝ እንዳንተ ያለ ጌታ አንተን መሳይ ወዳጅ እንዳንተ ያለ መሃሪ አንተን መሳይ አምላክ ለማወቅ ተከፈቱ ዓይኖቼ የመዳንን ቃል ሰምቼ ወስኜ አንተን ያገኘሁባት ያችን ቀን አልረሳት ያችን ቀን ልባርካት (2x) ውዴ ደጁን ሲያንኳኳ በሬን ከፈትኩለት ከእኔ ጋር እራት በላ የዋህ ነው በልቡ ትሁት ተቆረሰ የሕይወት እንጀራ ዓይኖቼም ተከፈቱ እንደንቦሳ ዘለልኩኝ አይረሳኝም ዕለቱ በዚያን ቀን አሃሃ ኃጢያቴ ተሰረየ በዚያን ቀን ኦሆሆ በሰማይ ደስታ ሆነ በዚያን ቀን በአብ ቀኝ ተቀመጥኩኝ በዚያን ቀን አምላክን እኔ ወረስኩኝ እንዳንተ ያለ ጌታ አንተን መሳይ ወዳጅ እንዳንተ ያለ መሃሪ አንተን መሳይ አምላክ ለማወቅ ተከፈቱ ዓይኖቼ የመዳንን ቃል ሰምቼ ወስኜ አንተን ያገኘሁባት ያችን ቀን አልረሳት ያችን ቀን ልባርካት (2x) ይገርማል እኔን መውደድህ ይገርማል ይገርማል እኔን ማሰብህ ይገርማል (2x) ይገርማል እኔን መውደድህ ይገርማል እኔን ማሰብህ ይገርማል እኔን ማፍቀርህ ይገርማል (3x)
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection