ዛሬማ ዓይኔ ያየው በለጠ ጆሮዬ ከሰማው በላዬ ስለ ሾምኩህ ልቤን ኩራት አለው (2x) ንግሥናህን ሳስበው ውስጤ ተደንቀ መገረም ተሞላ አንድ ነህ ለሕይወቴ አላውቅም ከአንተ ሌላ የለኝም ከአንተ ሌላ እንዴት ያምራል እንዴት ውብ ነው ንጉሥ ወግህ ስርዓትህ ሆ ኧረ እንዴት ያምራል እንዴት ውብ ነው አገዛዝህ ቅን ነው ፍርድህ (2x) ልዩ ነህ አንተ አትጠገብም (4x) ልዩ ነህ አንተ አትጠገብም ልዩ ነህ አንተ አልጠገብኩህም (2x) ማለዳም ማለዳ አዲስነትህ ነው ልዩ ያደረገህ ዕድሜውን ከአንተ ጋራ ፈጅቶ የትኛው ሰው ለመደህ የትኛው ሰው ጠገበህ ከትላንትናው ዛሬ ከዛሬው ነገ ይለያል የክብርህ ነፀብራቁ ስለዚህ በልጠህብኛል ከአልማዝ ከወርቅ ከዕንቁ (2x) ጆሮዬ ድምጽን ሰምቶ አይጠግብም ዓይኔ ክብርህን አይቶ አይጠግብም ምላሴ ጽድቅህን አውርቶ አይጠግብም ቃላቴ አደናንቆህ አይጠግብም ልዩ ነህ አንተ አትጠገብም (4x) ልዩ ነህ አንተ አትጠገብም ልዩ ነህ አንተ አልጠገብኩህም (2x) እንዴት ያምራል እንዴት ውብ ነው ንጉሥ ወግህ ስርዓትህ ሆ ኧረ አንዴት ያምራል እንዴት ውብ ነው አገዛዝህ ቅን ነው ፍርድህ (2x) ተወዳዳሪ አቻ እና እኩያ የለህም ልዩ ነህ ለዘላለም (4x)