ትውስ ድቅን ይልብኛል አይኔ ላይ እየሱሴ መስቀሉ ላይ የተወጋው ጎኑን ደሙ የፈሰሰው እኔን ከሃጢያቴ ሊያጥበኝ ነው የቆሰለው ጀርባው የተገረፈው እኔን ከእግዚአብሔር ጋር ሊያስታርቀኝ ነው እንዴት ነው የምትወደኝ እንዴት ነው የምትወደኝ እንዴት ነው የምትወደኝ ምህረትህ ሰው አረገኝ ደምህ ሲፈስልኝ በቀራኒዮ ላይ እርግማኔን ስትወስድ ስትሞት መስቀል ላይ ያን ሁሉ አበሳ ያየኸዉ ለኔ ነው ማንም አላስገደደህ ፍቅር ይዞህ ነው ማንም አላስገደደህ ፍቅር ይዞህ ነው ፍቅር ያንተን ፍቅር ኢየሱስ የትም አላየሁት ማንም ላይ አላየሁት ልዩ ፍቅርህ ልዩ ፍቅርህ ልዩ ፍቅርህ ልዩ ፍቅርህ ባነበብኩት ብቻ አይድለም በሰማሁት ብቻ አይድለም ምሕረትህ እየተከተለኝ ስወድቅ እሱ አይደል ወይ የሚያነሳኝ ስደክም የሚያቆመኝ አንተ መልካም አንተ መልካም ነህ ኧረ አንተ መልካም አንተ መልካም ነህ መልካም ነህ መልካም ነህ አንተ መልካም ነህ ክበርልኝ አንተ የኔ ጌታ ክበርልኝ አንተ የኔ ወዳጅ x4 ትውስ ድቅን ይልብኛል አይኔ ላይ እየሱሴ መስቀሉ ላይ የተወጋው ጎኑን ደሙ የፈሰሰው እኔን ከሃጢያቴ ሊያጥበኝ ነው የቆሰለው ጀርባው የተገረፈው እኔን ከእግዚአብሔር ጋር ሊያስታርቀኝ ነው እንዴት ነው የምትወደኝ እንዴት ነው የምትወደኝ እንዴት ነው የምትወደኝ ምህረትህ ሰው አረገኝ