የእኔ ዓለሜ የአንተ ክብር ነው (፪) የእኔ ዓለሜ የአንተ መንፈስ ነው(፪)}(፪) የሰው ልጅ ምኞቱ ከፍታ ስኬቱ በመደረግ ያልፋል ሁሉም ነገር ከንቱ ሕይወት ተገለጠ ለእኔም በርቶልኛል ኢየሱስ አንተው ነህ ሌላ ምን ያሻኛል ከአንተ ሌላ አያምረኝም (፪) ከአንተ ውጪ አያምረኝም (፪) ናፍቆቴ ነህ ምኞቴ ነህ ጉጉቴ ነህ ሕይወቴ ነህ የለም እንደ አንተ የምወደው የለም እንደ አንተ የምናፍቀው(፪) በመንፈስ የሆነ ሰላም የሞላው ሀዘን የሌለበት የአንተ ዓለም ነው ዳግመኛ ብፈጠር ዕድሉን ባገኝ ኢየሱስ አንተ ነህ የምታጓጓኝ ከአንተ ሌላ አያምረኝም (፪) ከአንተ ውጪ አያምረኝም (፪) የእኔ ዓለሜ የአንተ ክብር ነው (፻)