Song Lyrics

እረኛዬ ነው

ግዚአብሔር እርኛየ ነው ሚያሳጣኝ የለም የማጣው የለም የማጣው የለም እግዚአብሔር ፀጥታየ ነው ሚያውከኝ የለም ሚያውከኝ የለም X2 የማመልከው አምላክ የተደገፍኩት ጠበቀኝ እንዳልጠፋ እኔ እንዳልሞት በጆቹ መዳፍ ላይ ስለቀረፀኝ አልጠፋም የሚራራ አባት አለኝ የማያስደፍር ቅጥር ሆኖኛል መተማመኛ ማስፈራራቱም አያገኘኝም የዛ ቀማኛ የሚጠብቀኝ የኔ አባት አይሰለቸውም ቀንም ሌሊትም የሚጠብቀኝ የኔ እረኛ ቀኑን ጠብቆ ማታ ማይተኛ በቀኘ ነህና እኔ አልደነግጥም ሁልጊዜ ስለማይህ አልታወክም ከመከራ ስጋት ልቤ እርፍ ብሏል ሕይወቴ በጅህ ላይ ነው ምን ያስፈራኛል የማያስደፍር ቅጥር ሆኖኛል መተማመኛ ማስፈራራቱም አያገኘኝም የዛ ቀማኛ የሚጠብቀኝ የኔ አባት አይሰለቸውም ቀንም ሌሊትም የሚጠብቀኝ የኔ እረኛ ቀኑን ጠብቆ ማታ ማይተኛ እኔ የምኖረው አንተን ታምኜ ነው x2 በሕይወት የምኖረው ቃልህን ታምኜ ነው x2 እግዚአብሔር እርኛየ ነው ሚያሳጣኝ የለም የማጣው የለም የማጣው የለም እግዚአብሔር ፀጥታየ ነው ሚያውከኝ የለም ሚያውከኝ የለም
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection