Song Lyrics

አመሰግናለው

Ruth Tadesse
Semayawi Zeginet
አዝ:- አመሰግናለው (2x) ያረክልኝ ለእኔ ከአይምሮዬ በላይ ነው የሆንክልኝ ለእኔ ከአይምሮዬ በላይ ነው ሕይወትን ሰጥተኀኝ በመስቀል ላይ ሞትክና ዋጋዬን ከፈልክልኝ አስታረቅከኝ ከአብ ጋር በኀጢአት የጠፋውን ያጣሁትን ማንነቴን አገኘሁት በአንተ ሆነኅልኝ መስዋእቴ ሚስጥርህን ገለጥክልኝ መጥተህ መንፈስ ቅዱስ ኢየሱሴን አምኜው ወስኜ ስቀበል ከዛ ቃልህን ከፍቼ መረዳት ስጀምር ለእኔ ያሰብከው ሁሉ ይገለጥልኝ ጀመር አዝ:- አመሰግናለው (2x) ያረክልኝ ለእኔ ከአይምሮዬ በላይ ነው የሆንክልኝ ለእኔ ከአይምሮዬ በላይ ነው እንዴት ብዬ ዝም ልበል አስቸገረኝ መደበቁ የበራልኝ እውነት እኮ ያስገርማል ከሌሎቹ እንዴትስ ይደበቃል ኧረ መቼ ተችሎ ለብዙዎች ሚስጥር ሲሆን ሳየው ለእኔ ግን ተገልጦ አዝ:- አመሰግናለው (2x) ያረክልኝ ለእኔ ከአይምሮዬ በላይ ነው የሆንክልኝ ለእኔ ከአይምሮዬ በላይ ነው የበላይ እግዚአብሔር የለም አንተን ሚመስልህ ገና እስከዘለዓለም አንተ ትመለካለህ አመታት ተሰጥተውኝ ብናገር ብጨምር እንዴት ብዬ አውርቼ ስለአንተ ልፈጽም አዝ:- አመሰግናለው (2x) ያረክልኝ ለእኔ ከአይምሮዬ በላይ ነው የሆንክልኝ ለእኔ ከአይምሮዬ በላይ ነው
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection