Song Lyrics

አዶናይ

Ruth Tadesse
Semayawi Zeginet
ከሰማይ ነበር የተላከ ከሰው ተወልዶ ለሰው ሞተ ከሞት ተነሳ ከእዛ አረገ ከአባቲ ቀኝ ተቀመጠ ለዘመናት ቀል የነበረ ከእቅፉ ወጥቶ መጥቶ ተረፈ አባትን ከልጅ ያስታረቀ ከኢየሱስ ሌላ ጌታ የታለ አሃሃ አዶናይ (4x) የለም እንዳንት ምድር ላይ የለም እንዳንተ በሰማይ (2x) ለሁለት ጌቶች ለመገዛት ህጉ አይፈቅድም ይከለክላል አንዱን ይይዛል ያን ይተዋል ለፈቀደለት ባርያ ይሆናል ሚስጥሩ ገብቶኝ መረጥኩኝ ሌላውን ትቼ እርሱን ሾምኩኝ ኢየሱስ ጌታ ሲሆንልኝ የቀረው በሥሙ ተገዛልኝ ኢየሱሴ በእኔ ላይ (4x) አድርጌሃለሁ የበላይ (4x) እስኪ የቱ ነው የትኛው በፊቱ ከብዶ ሚታየው ሁሉን ይችላል ብቃት አለው ስለእግዚአብሔር ነው የምናገረው እኔም አየሁት በሕይወቴ ተዛዝ አውትቶ ሲሰራ አንዴ ታሪክ ሲነበብ ቀን ሲታይ እርሱ ብቻ ነው አልሻዳይ አይ ኤሄሄ አልሻዳይ (4x) የለም እንዳንት ምድር ላይ የለም እንዳንተ በሰማይ (2x)
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection