Song Lyrics

ቅርቤ ነህ

Ruth Tadesse
Semayawi Zeginet
ሰማያትን ቀና ብዬ እንደማይ ሳየውም ሩቅ እንደሆነ አምላኬ እንደእዛ አላይህም እግዚአብሔር እንደእዛ አላርቅህም ቅርብ ነህ ለእኔ አለህ አጠገቤ (4x) ሰማይ ሰፋህ አልለው ትልቅ ነህ ጌታዬ ግን መረጥክ ልትገባ ልትቆይ ከልቤ የታሰበ ኧረ ነው ለአንተ የተዘጋጀ ስለዚህ አውቃለሁ አጠገቤ እንዳለህ አዝ:- ቅርቤ ነህ ከጐኔ ነህ (2x) ይሰማኛል ህልውናህ (2x) የጠየኳቸው ጥያቄዎች ሁሉ መልስን ብትሰጣቸው ወይም ቢዘገዩ እነሱንም አይቼ ቅርቤ አላልኩህም እስከ ፍጻሜ ከእኔ ጋር ነህ አመንኩት ቃልህን አዝ:- ቅርቤ ነህ ከጐኔ ነህ (2x) ይሰማኛል ህልውናህ (2x)
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection