ምን አጣሁኝ ብለህ ወጣህ ከአባትህ ቤት ሄድክ ርቀህ ሰላም ደስታ ወደ ሌለበት አባትህ አሁንም እቤት ካሉት ይልቅ ያሰባል ሰለአንተ ይናፍቃል ይጠብቃል ሚመለሰው ልጄ መቼ ነው እያለ የጠፋው የእግዚአብሔር ልጅ አንተ አይደለህ ወይ መመለስህን ሁልጊዜ ይናፍቃል ሊያይ መመለስህን ሁልጊዜ እግዚአብሔር ይናፍቃል ሊያይ ና ተመለስ ሁሉን ትተህ እርሳውና የአባትህ እጅ ዛሬም ለአንተ ነው እንደተዘረጋ በትር ይዞ እኮ አይደለም ሚጠብቅህ ታውቀዋለህ አንዳይለወጥ እግዚአብሔር እንደሚወድህ ወንድሜ ብዙዎች በቤቱ ቢኖሩም ስለጠፋኀውስለአንተ ዘወትር ያስባል ወደ ቤቱ የምትመለስበትን ሰዓት ይጠባበቃል የክብር ልብስ ሊያለብስህ የምህረት ደጆቹ ሁልጊዜ ለአንተ ክፍት ናቸው በአባትህ ቤት መኖር ለአንተ ይሻልሃል ወስነህ እንዲ በል ኢሄው መጣሁ ወደ ቤት ተመልሻለሁ እንድትምረኝ በክርስቶስ አስቀድሜ ተይቃለሁ እኔም ልጅህ ናፍቄያለሁ አባቴ አንተን ይሄው ልጅህ መጥቻለው ብትቀበለኝ ወድሃለሁ (2x) እግዚአብሔር ወስኛለሁ አዲስ ጉዦ ከአንተ ጋራ ልጀምር ወስኛለሁ አዲስ ጉዦ ከአንተ ጋራ ልጀምር