Song Lyrics

አዋቂ ነህ

Ruth Tadesse
Semayawi Zeginet
አዝ:- አዋቂ ነው የኔ ጌታ አዋቂ ነው (5x) አዋቂ ነው እግዚአብሔር አዋቂ ነው ጽንሷ መዘግየቱ ያሳዝናል ሃና ባትረዳ ባይገባት ጌታ በእርሷ ያየው ትልቅ ሰው አስቦ ነው እንጂ ለእራሱ ሊለየው ረስታ ሃና የእግዚአብሔርን አዋቂነት ካሰበችው በላይ ሲሆን ድንገት የእርሱ ስራው ለጊዜ አስደናቂ አለች እርሷም ግርም ሲላትኧረ አዋቂ አዝ:- አዋቂ ነው የኔ ጌታ አዋቂ ነው (5x) አዋቂ ነው እግዚአብሔር አዋቂ ነው ኤልያብ ነው በሰው ሚዛን የበለጠው በነቢዩ ዐይን እንኳን ቀድሞ የገባው ፊትን አልፎ ሚመረምር የልብን እግዚአብሔር ግን መረጠው ዳዊትን የጓዳውን ሰው ሳያየው ስለሚያውቀው እረኛውን በስልጣን ላይ አስቀመጠው ጠብቆ ሁሉን ነገር ስለሚያውቀው ሲመርጥ እርሱ አይሳሳትም አዋቂ ነው አዝ:- አዋቂ ነው የኔ ጌታ አዋቂ ነው (5x) አዋቂ ነው እግዚአብሔር አዋቂ ነው የትኛውን ነገሬን ነው ምደብቀው እግዚአብሔር ሁሉን ያያል አዋቂ ነው በሰዎች መመረጥ ቀርቶብኝ ይሁንልኝ እግዚአብሔር ያየልኝ ጅማሬውን ፍጽሜውን ስለሚያውቀው ይሻለእኛል ምንም ቢሆን እርሱ ያለው መልካም ስለሆነ የሚያስበው የመረጠው እርሱ ለእኔ ምርጫዬ ነው አዝ:- አዋቂ ነው የኔ ጌታ አዋቂ ነው (5x) አዋቂ ነው እግዚአብሔር አዋቂ ነው
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection