አዝ:- እቀድስሃለው እግዚአብሔር አምላኬ በውጪ አይደለም ማደሪያህ ገብቼ ገብቼ (2x) ድሮ ትዝ ይለኛል በፊት ገና ያኔ መስዋእቴን ለካህንህ ስሰጥ እኔ ውጭ ቆሜ ካህኑ የገባው እየቀደሰህ እኔም እመኝ ነበር ክብርህን ማየት ዛሬማ ሆነልኝ እኔም በልጅህ ደፍሬ እንድገባ ወደ መገኛህ አዝ:- እቀድስሃለው እግዚአብሔር አምላኬ በውጪ አይደለም ማደሪያህ ገብቼ ገብቼ (2x) ብዙዎች ያመልካሉ ስለማያውቁት ስፍራን ይመርጣሉ ለማቅረብ ለአንተ ስግደት እኔ ግን እያወኩ ገብቶኝ ማንነትህ በመንፈስ በእውነት ወደድኩኝ ላመልክህ ካህን አልፈልግም ረዳትስ ለእኔ እቀድስሃለሁ ብቻዬን መጥቼ አዝ:- እቀድስሃለው እግዚአብሔር አምላኬ በውጪ አይደለም ማደሪያህ ገብቼ ገብቼ (2x) መስዋእት አለ ከኔ ለአንተ ምሰጥህ ስለ አደረክልኝ አይደል ገብቶኝ እንጂ ማንነትህ በግሌ አወቅኩህ ወደድኩህ ከልቤ በማወቅ ተናገርሁ አምላኬ ነህ ብዬ በማወቅ ተናገርሁ አዳኜ ነህ ብዬ በማወቅ ተናገርሁ ጌታዬ ነህ ብዬ አዝ:- እቀድስሃለው (3x) ጌታዬ በውጪ አይደለም ማደሪያህ ገብቼ ገብቼ (2x)