Song Lyrics

ትልቅ አንተ ብቻ

Ruth Tadesse
Semayawi Zeginet
አዝ:- ትልቅ አንተ ብቻ ነህ ትልቅ ትልቅ (4x) አይችልም ምንም ማንም ከአንተ ሊልቅ (4x) ጉልበተኛ ነው ከተባለ ምንም ነገር ተለካክቶ ነው ተወዳድሮ ከሌላው ጋር አንተ ምድርን ሰማያትን እንኳን ስጸራ የተጠቀምከው ቃልህን ነው ከአፍህ የወጣ ቃልህ ያልተፈጠረውን መፍጠር ከቻለ እንዴት ትልቅ ነው ነገርህ ልበል ልናገር ለአንተ አዝ:- ትልቅ አንተ ብቻ ነህ ትልቅ ትልቅ (4x) አይችልም ምንም ማንም ከአንተ ሊልቅ (4x) የአንተ የሆኑት ልጆችህ ከአንተ የወጡት ቃልህን በውስጥ መንፈሳቸው ስላስቀመጡት እነርሱ ሳይቀር የአንተን ቃል ሲናገሩት ስጋን ተላብሰው ሰራዊት ሆኗል ደረቅ አጥንት ዝናብ እንዳይወርድ ተከልክሎ ፀሐይ ቆማለች አይደለም አንተ ልጆችህ ናቸው ሃይለኞች አዝ:- ትልቅ አንተ ብቻ ነህ ትልቅ ትልቅ (4x) አይችልም ምንም ማንም ከአንተ ሊልቅ (4x) ቀላል ነው በአንተ እይታ ሳየው ይሆናል ቃል ስትወጣ ወዲያው ባለ ስልጣን ነህ እግዚአብሔር ባለስልጣን ግር ግር የለም ስትናገር ሁሉ ይሰማል ይሆንልሃል እንደአፍህ አንተ እንዳልከው ስላመንኩብህ አንተን ነው የማመልከው አዝ:- ትልቅ አንተ ብቻ ነህ ትልቅ ትልቅ (4x) አይችልም ምንም ማንም ከአንተ ሊልቅ (4x)
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection