Song Lyrics

ትዝ ይለኛል ቀኑ

Ruth Tadesse
Semayawi Zeginet
(ትዝ ይለኛል) አዝ:- ትዝ ይለኛል ቀኑ (2x) ትዝ ይለኛል በደምብ ከሞት የተረፍኩበት አስቤ አላደረኩት ቀጠሮም አልነበረኝ በድንገት በአጋጣሚ በስፍራው ተገኘሁኝ (ትዝ ይለኛል ቀኑ) ወደቤተ መቅደሱ ወደውስጠኛው ስገባ ተሰማኝ የእግዚአብሔር የአምላኬ ህልውና (ትዝ ይለኛል ቀኑ) አዝ:- ትዝ ይለኛል ቀኑ (2x) ትዝ ይለኛል በደምብ ከሞት የተረፍኩበት ሰሰማን ህልውናው በደስታ ውስጤ ሲሞላ ከዐይኖቼ ሲፈሱ የደስታ የሃሴት እምባ (ትዝ ይለኛል ቀኑ) እጆቼን ዌርሱ አንስቼ በቃ የአንተ ነኝ ስለው ለዘለዓለም ወስኜ ሕይወቴን ስሰጠው (ትዝ ይለኛል ቀኑ) አዝ:- ትዝ ይለኛል ቀኑ (2x) ትዝ ይለኛል በደምብ ከሞት የተረፍኩበት አንደበቴ ለክብርህ መከፈት ሲጀምር ሰዎችም ሲደነቁ በአደረክልኝ ነገረ (ግርም ይለኝ ጀመር) ይቅርታን ከአንተ ጠይቄ ምህረትህ በዝቶልኝ እንደገና በቤትህ አጽንተህ ስትተክለኝ (እጅግ ተደሰትኩኝ) አዝ:- ትዝ ይለኛል ቀኑ (2x) ትዝ ይለኛል በደምብ ከሞት የተረፍኩበት ማንነቴ ተቀይሮ አዲስ ፍጥረት ሆንኩኝ የኋላዬን ረስቼ የፊቴን እያየሁኝ (ጉዞዬን ጀመርኩኝ) ድል በድል እየጨመረ ነገሬ እያማረልኝ የሚያውቀኝ ሰው በሙሉ ሲገረም ሲደነቅብኝ (ጌታዬን አከበርኩኝ) አዝ:- ትዝ ይለኛል ቀኑ (2x) ትዝ ይለኛል በደምብ ከሞት የተረፍኩበት
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection