Song Lyrics

ሰማያዊ ዜግነት

Ruth Tadesse
Semayawi Zeginet
አዲስ ልዩ ነገድ ተገኝቷል ከአስራ ሁለቱ አይደል ከእስራኤል (2x) እጅግ ልዩ ነው ዐይነቱ የነገዱ ሃያል ገናና ነው ንጉሡ የጸና መንግሥቱ (2x) ዜግነት ቢሉ ሰማያዊ አለቃው የሰማይ የምድር ፈጣሪ አለ የሚኖር ዘለዓለማዊ አዝ:- (አስገረመኝ አስደነቀኝ) ወደዚህ መንግሥት ሲጋብዘኝ (አስገረመኝ አስደነቀኝ) አዲስ ዜግነት እስኪሰጠኝ (አስገረመኝ አስደነቀኝ) ወደዚህ ግዛት ሲጋብዘኝ (አስገረመኝ አስደነቀኝ) አዲስ ማንነት እንዲሰጠኝ እኔም ግዛቱ ለመግባት አሰብኩኝ ህገመንግሥቱን አነበብኩኝ የተጻፈውን አንበብኩኝ መግቢያው መወለድ ነው ዳግም የመስቀሉን ሃይል አምኖ መቀበል (2x) መቀበል ማመን በልጁ በመንፈስ ዳግም መወለዱ ሌላም አይደለም ይሄው ነው መንገዱ አዝ:- (አስገረመኝ አስደነቀኝ) በማመን ብቻ ሲቀበለኝ (አስገረመኝ አስደነቀኝ) ልጁን ስቀበል ተ???በለኝ (አስገረመኝ አስደነቀኝ) አባቴ ሆኖ ልጄ ሲለኝ (አስገረመኝ አስደነቀኝ) ለዘለዓለም ኑሪ ሲለኝ ጽዮናዊ ነኝ በዜግነት አሁንማ ተረሳስተናል ከዓለም ጋራ ተካክደናል ከዓለም ጋራ ሰማያዊ ነው ሚናፍቀኝ የማስበው የምድርን ንቄ ትቼዋለሁ ጽዮንን ተመኘሁ (2x) ጨለማው ጠፍቶ በርቻለሁ ሰማያዊ ነው የምናገረው ስፍራ ቀይሬ በቀኙ ሆኛለሁ አዝ:- (አስገረመኝ አስደነቀኝ) በቀኙ በኩል አስቀመጠኝ (አስገረመኝ አስደነቀኝ) ቋንቋዬን ሁሉ ቀየረልኝ (አስገረመኝ አስደነቀኝ) አዲስ ማንነት አገኘሁኝ (አስገረመኝ አስደነቀኝ) ወደ መንግሥቱ ገላገለኝ
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection