Song Lyrics

የእግዚአብሔር ቃል

Roman Samuel
Negeru Tegelebete
ሃብቴ ነው ሃብቴ ሃኪሜም መድኃኒቴ ከሞት ጉዞ መለሰኝ በሕይወት ጐዳና መራኝ ዝናብ ምድርን እንዲያርስ ውስጤን አረስርሶታል ለአምላኬ ክብር እንድኖር ለፅድቅ አነቃቅቶኛል የእግዚአብሔር ቃል ይባረክ (4x) . (1) . አስደነቀኝ ፈተሸኝ መረመረኝ ከክፉ . (2) . መክሮ በልቤ ተሰውሮ ማስተዋሌን አስፈትቶ በትዕዛዙ ሮጣለሁ የእለት መመሪያዬ አስተዳዳሪዬም ነው የእግዚአብሔር ቃል ይባረክ (4x) ከመጻሐፍት በኩር ታላቅ መጽሐፍት የማይለወጥ የማይሻር መጽሐፍ ቅዱስ የአምላኬ ቃል (2x) ከሐዘን መጽናኛዬ ቀን ሙሉ ትዝታዬ ሆኖኝ ወድጄዋለሁ ዘወትር አጫዋቼ ነው ስስት ይገስፀኛል ስዝል ያበረታኛል ከስንቁ በልጦብኛል ነፍሴን ሕያው አድርጓታል ለእግሬ ምብራት ነው ለመንገዴም ብርሃን ነው ከየት እንደተገኘሁ ለምን በምድር እንዳለሁ በኋላም መድረሻዬን አሳየኝ ገልጦ ዓይኔን ቁም ነገረኛ አድርጐ ውብ ዓላማ አስጨበጠኝ እንደ ሌላ ለውጦ ከሰውም ሰው አረገኝ የእግዚአብሔር ቃል ይባረክ (4x) ከመጻሐፍት በኩር ታላቅ መጽሐፍት የማይለወጥ የማይሻር መጽሐፍ ቅዱስ የአምላኬ ቃል (2x) እንዱ ከድኖ ሲስመው ሌላው ሲንተራስበት አንዱ ተረት ሲመስለው ሌላው ሲያላግጥ ለእኔ ግን ሆኖኛል የማይዘለቅ በረከት (2x) ብሰማው ብሰማው ማዳምጠው ማዳምጠው ሁሌ አዲስ ነው ሁሌ አዲስ ነው ባነበው ባነበው ባጠናው ባጠናው የእግዚአብሔር ቃል ይባረክ (4x) ከመጻሐፍት በኩር ታላቅ መጽሐፍት የማይለወጥ የማይሻር መጽሐፍ ቅዱስ የአምላኬ ቃል (2x)
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection